Jeremiah 50

ስለ ባቢሎን የተነገረ መልእክት

51፥15-19 ተጓ ምብ – ኤር 10፥12-16 1 እግዚአብሔር ስለ ባቢሎንና ስለ ባቢሎናውያን
ወይም ከለዳውያን፤ በ8፡25፡35 እና 45 ይመ።
ምድር፣ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

2“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤
ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤
አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤
‘ባቢሎን ትያዛለች፤
ቤል ይዋረዳል፤
ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤
ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤
አማልክቷም ይሸበራሉ።’
3ከሰሜን አንድ መንግሥት መጥቶ ይወጋታል፤
ምድሯንም ባድማ ያደርጋል፤
የሚኖርባትም አይገኝም፤
ሰዎችና እንስሳትም ሸሽተው ይሄዳሉ።

4“በዚያ ዘመን፣ በዚያ ጊዜም፤”
ይላል እግዚአብሔር
“የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ፤
አምላካቸውንም እግዚአብሔርን በመፈለግ እያለቀሱ ይመጣሉ።
5ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤
ፊታቸውንም ወደዚያ ያቀናሉ።
መጥተውም ከቶ በማይረሳ፣
በዘላለም ቃል ኪዳን፣
ከእግዚአብሔር ጋር ይጣበቃሉ።

6“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤
እረኞቻቸው አሳቷቸው፤
በተራሮችም ላይ እንዲቅበዘበዙ አደረጓቸው፤
በተራራና በኰረብታ ላይ ተንከራተቱ፤
ማደሪያቸውንም ረሱ።
7ያገኛቸው ሁሉ ይውጣቸዋል፤
ጠላቶቻቸውም፣ ‘እኛ በደለኞች አይደለንም፤
እነርሱ የአባቶቻቸውን ተስፋ እግዚአብሔርን፣
እውነተኛ ማደሪያቸው የሆነውን እግዚአብሔርን በድለዋል’ አሉ።

8“ከባቢሎን ሽሹ፤
የባቢሎናውያንን ምድር ልቀቁ፤
መንጋ እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ።
9የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣
ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤
እነርሱም በእርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤
መጥተውም ይይዟታል።
ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣
እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።
10የባቢሎን ምድር
ወይም ከላውዴዎን
ትዘረፋለች፤
የሚዘርፏትም ሁሉ እስኪበቃቸው ይመዘብሯታል፤”
ይላል እግዚአብሔር

11“እናንተ ርስቴን የበዘበዛችሁ ሆይ፤
ደስ ስላላችሁና ሐሤትም ስላደረጋችሁ፣
በመስክ እንዳለች ጊደር ስለ ፈነጫችሁ፤
እንደ ድንጉላ ፈረስ ስለ አሽካካችሁ፤
12እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፤
የወለደቻችሁም ትዋረዳለች።
እርሷም ምድረ በዳ፣ ደረቅ ምድርና በረሓ፣
ከመንግሥታትም ሁሉ ያነሰች ትሆናለች።
13 ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ፣
የሚኖርባት አይገኝም፤
በቍስሎቿም ሁሉ ምክንያት፣
በባቢሎን የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ ያፌዝባታልም።

14“እናንተ ቀስት የምትገትሩ ሁሉ፣
በባቢሎን ዙሪያ ተሰለፉ፤
አንዳች ሳታስቀሩ ፍላጾችን ስደዱባት፤
በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታለችና።
15ከየአቅጣጫው ጩኹባት፤
እጇን ትሰጣለች፤ ምሽጓም ይወድቃል፤
ቅጥሮቿ ይፈርሳሉ።
ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና፣
እርሷን ተበቀሏት፤
በሌሎቹ ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።
16ከባቢሎን ዘር የሚዘራውን፣
በመከር ጊዜ ማጭድ የጨበጠውንም ዐጫጅ አጥፉት፤
ከአጥፊው ሰይፍ የተነሣ፣
እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለስ፤
ወደ ገዛ ምድሩም ይሽሽ።

17“እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣
የተበተነ መንጋ ነው፤
መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣
ቦጫጭቆ በላው፤
በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣
ዐጥንቱን ቈረጣጠመው።”
18ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁት ሁሉ፣
የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።
19እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤
በቀርሜሎስና በባሳን ላይ ይሰማራል፤
በኤፍሬም ተራሮችና በገለዓድም ላይ፣
እስኪጠግብ ይመገባል።
20በእነዚያ ጊዜያት፣ በዚያ ዘመን፣”
ይላል እግዚአብሔር
“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤
አንዳችም አይገኝም፤
የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፤
ከቶም የለም፤
እንዲተርፉ ያደረግኋቸውን ቅሬታዎች እምራለሁና።

21“የምራታይምን ምድር፣
የፋቁድ ነዋሪዎችንም፣
አሳድዷቸው፤ ግደሏቸው፤ ፈጽማችሁም አጥፏቸው፤”
አጥፏቸው ለሚለው የሚተካው የዕብራይስጡ ቃል የሚያመለክተው ነገሮችን ወይም ሰዎችን ዳግም ላይመለሱ ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መስጠትን ነው፤ 26 ይመ።

ይላል እግዚአብሔር
“ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ።
22በምድሪቱ የጦርነት ውካታ፣
የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰማ።
23የምድር ሁሉ መዶሻ፣
እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ ደቀቀ!
በሕዝቦች መካከል፣
ባቢሎን እንዴት ባድማ ሆነች!
24ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤
አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤
እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣
ተገኘሽ፤ ተያዝሽም።
25 እግዚአብሔር የመሣሪያ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤
የቍጣውን የጦር ዕቃ አውጥቷል፤
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
በባቢሎናውያን ምድር ሥራ አለውና።
26ከሩቅ መጥታችሁ በእርሷ ላይ ውጡ፤
ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤
እንደ እህል ክምር ከምሯት፤
ፈጽማችሁ አጥፏት፤
ምኗም አይቅር።
27ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤
ወደ መታረጃም ይውረዱ!
የሚቀጡበት ጊዜ፣
ቀናቸው ደርሷልና ወዮላቸው!
28 እግዚአብሔር አምላካችን የተበቀለውን፣
ስለ ቤተ መቅደሱ የተበቀለውን በቀል፣
ከባቢሎን የመጡ ኰብላዮችና ስደተኞች፣
በጽዮን የሚናገሩትን ስሟቸው።

29“ቀስት የሚገትሩትን፣
ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩ፤
አንድም ሰው እንዳያመልጥ፣
ዙሪያውን ሁሉ መሽጉ፤
የእስራኤልን ቅዱስ፣
እግዚአብሔርን አቃልላለችና፣
እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤
በሌሎች ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።
30ስለዚህ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤
በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤”
ይላል እግዚአብሔር
31“አንተ ትዕቢተኛ፤ እነሆ፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤”
ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
“የምትቀጣበት ጊዜ፣
ቀንህ ደርሷልና።
32ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤
የሚያነሣውም የለም፤
በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣
በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።”
33የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ፣
በአንድነት ተጨቍነዋል፤
የማረኳቸውም ሁሉ አጥብቀው ይዘዋቸዋል፤
ይለቅቋቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል።
34ነገር ግን ቤዛቸው ብርቱ ነው፤
ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤
ለምድራቸው ዕረፍትን ለመስጠት፤
ተግቶ ይሟገትላቸዋል፤
በባቢሎን የሚኖሩትን ግን ዕረፍት ይነሣቸዋል።

35“ሰይፍ በባቢሎናውያን ላይ መጣ!”
ይላል እግዚአብሔር
“በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ፤
በባለሥልጣኖቿና በጥበበኞቿም ላይ ተመዘዘ!
36ሰይፍ በሐሰተኞች ነቢያቷ ላይ መጣ!
እነርሱም ሞኞች ይሆናሉ፤
ሰይፍ በጦረኞቿ ላይ ተመዘዘ፤
እነርሱም ይሸበራሉ።
37ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣
በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ!
እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤
ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ!
ለዝርፊያም ይሆናሉ።
38ድርቅ
ወይም ሰይፍ
በውሆቿ ላይ መጣ!
እነሆ፤ ይደርቃሉ፤
ምድሪቱ በፍርሀት በሚሸበሩ አማልክት፣
በጣዖትም ብዛት ተሞልታለችና።

39“ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣
የጕጕትም ማደሪያ ትሆናለች፤
ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤
ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም።
40 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፣
በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀራቸው”
ይላል እግዚአብሔር
“እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤
የሚቀመጥባትም አይገኝም።

41“እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤
አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣
ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል።
42ቀስትና ጦር ይዘዋል፤
ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤
በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣
ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ ያስገመግማል።
አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤
ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።
43የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነርሱ ሰማ፤
እጆቹም በድን ሆኑ፤
ጭንቀት ይዞታል፤
ምጥ እንደ ያዛት ሴት ታምሟል።
44አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች ድንገት ወጥቶ፣
ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣
እኔም ባቢሎንን ሳይታሰብ ከምድሯ አባርራታለሁ፤
የመረጥሁትንም በእርሷ ላይ እሾማለሁ፤
እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል?
የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”

45ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደውን፣
በባቢሎናውያንም ምድር ላይ ያሰበውን ስሙ፤
ከመንጋው ታናናሹ ተጐትቶ ይወሰዳል፤
በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።
46በባቢሎን ውድቀት ድምፅ ትናወጣለች፤
ጩኸቷም በሕዝቦች መካከል ያስተጋባል።
Copyright information for AmhNASV